Get Mystery Box with random crypto!

Ëțhïø Ďaily šmart Phõťøgrãphř Zone

Logotipo do canal de telegrama ethio_photographr_yabuz - Ëțhïø Ďaily šmart Phõťøgrãphř Zone Ë
Logotipo do canal de telegrama ethio_photographr_yabuz - Ëțhïø Ďaily šmart Phõťøgrãphř Zone
Endereço do canal: @ethio_photographr_yabuz
Categorias: Não categorizado
Idioma: Português
Assinantes: 159
Descrição do canal

Photograhr,Edetor,Camera Man,Shooting photo,Famous,artisti.....edspz

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


As últimas mensagens

2021-05-02 00:48:41 “#ተነሥቶአል_በዚህ ፣ የለም” ማር. 16፡6 ።

እንኳን ለ2013 ዓ.ም. የጌታችንና የመድኃታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ በሰላም አደረሳችሁ !

“ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን አግዐዞ ለአዳም
ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍሥሐ ወሰላም ፤”

ትርጓሜ፡-

“ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ
ዲያብሎስን አሰረው ፤ አዳምን ነጻ አወጣው ።
ሰላም ! ከዛሬ ጀምሮ ደስታና ሰላም ሆነ ።” /ኦርቶዶክሳዊ አዋጅ/

. . .

በዓለም ላይ አንድ መቃብር ብቻ ባዶ ነው ። በጠባቆች የሚጠበቁ ብዙ መቃብሮች አሉ ። መቃብሩ እየተጠበቀ ግን ከተማውን የሞላ አንድ ብቻ ነው ። ተነሥተው ሕያው የሆኑ ሰዎችን አናውቅም ፣ ዳግም ሞት ላይዘው የተነሣውን ጌታ ግን እናውቃለን ። መግነዙን ቢያልፍ ፣ የተዘጋውን ቋጥኝ አያልፍም ፤ ቋጥኙን ቢያልፍ ወታደሮችን አያልፍም ፤ ወታደሮችን ቢያልፍ ገንዘብ የሚያስለፈልፋቸውን እውነትን ሐሰት የሚሉትን ማለፍ አይችልም ተብሎ ሳለ ምድርን የሞላው አንድ ብቻ ነው ። የሥጋውያንና የረቂቃንን ምክር ፣ የሲኦልና የሮማ ቤተ መንግሥትን ትብብር ፣ የቤተ ክህነትና የቤተ መንግሥትን ሽርክና ፣ የሊቀ ካህናትና የንጉሠ ነገሥትን ፊርማ አሸንፎ ልብን ግዛቱ ያደረገ አንድ ብቻ ነው ። እርሱም ከሞት የተነሣው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ።

እንደ እርሱ ሞት ያስገረመ ፣ እንደ እርሱ ትንሣኤ ያስደመመ የለም ። የማይሞተው ሲሞት “የምትወዱት አልቅሱለት” ተባለ ፣ በራሱ ኃይልና ሥልጣን ሲነሣ “ክብርና በረከት ይገባዋል” ተባለ ። መቃብሮች ሁሉ አጽሞች እንዳይሰረቁ ይጠበቁ ይሆናል ፣ እንዳይነሣ የሚጠበቅ መቃብር ግን የለም ።ክርስቶስ ግን እንዳይነሣ መቃብሩ ዘብ ቆመበት ፤ ከወዳጆቹ ይልቅ መነሣቱ በጠላቶቹ የታመነ ነበር ። ጠላቶቹ መሞቱንና መነሣቱን ቢያምኑም አልዳኑም ። ለመዳን ከእርሱ ጋር መሞትና መነሣት ያስፈልጋልና ። ገደልነው ብለው ደስ ይላቸዋል ፣ ወዲያው እነሣለሁ ብሏል እያሉ መረበሽ እንቅልፍ ይነሣቸዋል ። የማያስተኛ ሟች ፣ የማይያዝ የትንሣኤ ጌታ ነው ። መቅደስ እያከበሩ መቅደስ ሰውነቱን አፈረሱ ፣ የሦስት ቀን ድልን ፈቀደላቸው ። ያዘኑ ወዳጆቹ ይደሰቱ ዘንድ ፣ የተደሰቱ ጠላቶቹ ያፍሩ ዘንድ ክርስቶስ ተነሣ ። የእስራኤልን መነሣት ተስፋ እያደረጉ የሚያነሣትን ገደሉት ። እንደ አቅማቸው ከእንቅልፍ እየተነሡ እንደ አቅሙ ከሞት እንደሚነሣ ዘነጉ ። የኃጢአት አውራው ዝንጋዔ ነው ። አይቶ እንዳላየ መሆን ነውና ።

ወትሮም እነርሱ በመቅደስ ሆነው እርሱ በመንደር ሲያስተምር አላፈሩም ። ከመቅደስ ሳይሆን ከከተማው አውጥተው ሰቀሉት ። ዛሬም ክርስቶስ በደጅ ነው ፣ መቅደሱ በሰቃዮች ሲሞላ ክርስቶስ በደጅ ይኖራል ። በመቅደስ በአሮናዊ ሥልጣን ፣ በደጅ በሮማውያን ሥልጣን ከምድረ ገጽ ይጥፋ ብለው ተነሡ ። ከመቅደስ ቢያባርሩት መቅደሱ ፈረሰ ፣ ከከተማ ቢያባርሩት ኢየሩሳሌም ተደመሰሰች ። ከዓለም ቢያባርሩት ዓለም ምጥ ያዘው ። እውቀቱ ወደ አለማወቅ ተለወጠ ። የመግደል እውቀት የማዳን እውቀት መሆን አቃተው ። እርሱ ግን ሰማይ ቤቱ ፣ ምድር ግዛቱ ፣ ምእመን ርስቱ ነው ።

ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀን እንደ ቆየና ሕያው እንደ ነበረ ክርስቶስም በሙታን መንደር ሙታንን እየፈለገ ሕያው ነበር ። ዮናስን የጣሉ እንደ ሞተ ያውቃሉ ፣ የጣሉት ሳያዩት ንስሐ የገቡ አዩት ። ክርስቶስም ያረዱት ሳይበሉት ፣ ኃጢአተኛ ነን ያሉ ጠገቡት ። ዮናስ ከሦስት ቀን በኋላ ወደ ነነዌ በንስሐ ድምፅ መጣ ፣ ጌታም ወደ ነነዌ ዓለም “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” እያሉ ወደሚሄዱት ደቀ መዛሙርት መጣ ። ከትንሣኤ በኋላ ቂምና መተዛዘብ የለም ፣ ለካደው ጴጥሮስ ቅድሚያ ተገለጠ ፣ አፍሮ እንዳይጠፋበት ። ለማናፍረው እያፈረ ስንት ዘመን አባበለን ። የሸሹትን ደቀ መዛሙርት ሳይታዘብ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አለ ። እርሱ “የሰውን ድካም ያውቀዋልና” ። ሞት ፍቅሩን አልገደለበትም ። እኛ ጭረት ፣ ትንሽ ቍስል ፍቅራችንን ገድላብን ይኸው ተስፋ ቢስነት ያሰቃየናል ። ለይቅርታ ካልተነሣን ሳንነሣ እንቅር ። መነሣት ብቻ በቂ አይደለም ፣ ለምንድነው የተነሣነው ማለት ያስፈልጋል ። ጌታ ለይቅርታ ፣ ብዙዎች ለበቀል ተነሡ ።

ክርስቶስ ጊዜ ሰጥቶት አልተነሣም ፣ በራሱ ኃይል ተነሣ ። በእግዚአብሔር መንግሥት ጊዜ የሚባል ቸር የለም ፣ ሁሉን የሚያደላድል የመለኮት እጅ ነው ። ሰዎች ማደሪያ ከልክለውት በደብረ ዘይት ጫካ ያድር የነበረው ምድር ግን ለሦስት ቀን ሸሸገችው ። ገጣሚው፡-

“ሞት ይቅር ይላሉ ፣
ሞት ቢቀር አልወድም ፤
አፈሩም ድንጋዩም ከሰው ፊት አይከብድም” ያለው ለዚህ ነው ።

እርሱ በሥጋ ሞተ ፣ በመለኮቱ ግን ሕያው ነው ። ሰንበትን በመቃብር አከበረ ። የሕይወት ሰንበታችን ነውና ልናከብረው እንደሚገባን አስተማረን ። መነሣቱን አይሁድም ይጠብቃሉ ጦር ይዘው ፣ ቅድስት እናቱም ትጠብቃለች ምስጋና ይዛ ። አጠባበቃችን እንጂ መጠበቃችን ዋጋ አይሰጠውም ። እግዚአብሔር ወራጁን ትቶ ምንጩን ያያል ። ሰው ግብዝ ነውና ወራጁን እያየ ያብዳል ። የእግዚአብሔር ልጅን መቃብር ከሦስት ቀን በላይ አልቻለውም ። በፈቃዱ ሞተ ፣ ተቀበረ ። ጠባቂዎቹ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ብቻ እንዲጠብቁ ታዘዙ ። በአይሁድ ልማድ ሦስተኛው ቀን ሞት እርግጥ የሚሆንበት ነው ። ጌታችን ግን ሞት እርግጥ በሚሆንበት ቀን ትንሣኤውን እርግጥ አደረገ ። እርሱ ባይነሣ ኑሮ ሐዋርያት አፍረው ወደ ገሊላ ይመለሱ ነበር ። እርሱ ባይነሣ ኑሮ ሐዋርያት ተነሣ በማለታቸው ወንጀለኛ ተብለው መከሰስ ሳይሆን አበዱ ተብለው መታከም ይኖርባቸው ነበር ። የሚከሰስም ጤነኛ ነውና ።

የምታምኑት እስኪ እልል በሉለት ። ምንድነው ዝምታው ? ስለ ሞት እያወራችሁ ስለ ሕያው ጌታ ምነው ዝም አላችሁ ? ጌታ ሆይ ተነሥተሃል አምናለሁ ። አይሁድ በጥፊ የመቱትን ጉንጭህን እስመው ዘንድ ወዴት አገኘዋለሁ ? ከበው ርኩስ ምራቃቸውን የተፉብህ ከብቦ የሚያስጨንቀንን በትንሣኤህ ጉልበት በትነው ።

፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ጸሎት ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨

ቅድስት ሞትህን ቡርክት ትንሣኤህን አምናለሁ ፣ እባክህ ጽድቄን ይቅር በለው ። ፎቶ የሚያነሣ ይዤ እመጸውታለሁ ፣ መልክ ቀራጭ አቁሜ ስግደት እሰግዳለሁ ። ለዝና ደግ ነኝ ፣ ለወሬ ሰጪ ነኝ ። ዛሬ ኃጢአቴን ሳይሆን ጽድቄን ይቅር በለው ። ክፉ መስሎ የሚከፋውን ሁሉ ይጠላዋል ፣ ደግ መስሎ መክፋትን አንተ ትጠላዋለህ ። እባክህን ግብዝነት ያሸተተውን ይህን ሁሉ ሬሣ አንሣው ። አደራህን ብቻህን እንዳትነሣ የሞተ ወገንህን ይዘህ ተነሣ ። ታርደህ በጽዮን ለቆምከው በግ ምስጋና አቀርባለሁ ። በማይፈጸም ዘመን ለዘላለሙ አሜን ።
188 views21:48
Aberto / Como
2020-11-14 20:59:12 https://t.me/KIMI_LULE
705 views17:59
Aberto / Como
2020-11-04 20:30:18
781 views17:30
Aberto / Como
2020-11-01 16:59:18
portraits Aroun the church .
Hey it's Me a channel if u want to post ur pic's & cross channels... contact me @YSuperMe
@Ethio_photographr_Yabuz
The Weeknd

Photographer

Join
@Ethio_photographr_Yabuz
2.5K views13:59
Aberto / Como
2020-11-01 16:43:27
Streets of piassa
Shoe shiner
.
.
.
@Ethio_photographr_Yabuz
534 views13:43
Aberto / Como
2020-11-01 16:37:28
Streets of merkato
.
.
.
.
https://t.me/Ethio_photographr_Yabuz
449 views13:37
Aberto / Como
2020-11-01 16:28:32
Rain In Addis Abeba . . . https://t.me/Ethio_photographr_Yabuz
420 views13:28
Aberto / Como
2020-11-01 13:34:48 https://t.me/KIMI_LULE
382 views10:34
Aberto / Como
2020-10-30 16:21:47
https://t.me/Ethio_photographr_Yabuz
397 views13:21
Aberto / Como
2020-10-19 20:34:33 Fikerent ethiopia net kuratnet new Ethiopia Lezelalem tunure https://t.me/Ethio_photographr_Yabuz
568 views17:34
Aberto / Como